በኢትዮጵያ ለደረሰው የቦይንግ 737 ማክስ የአውሮፕላን አደጋ የካሳ ክስ ችሎት ቺካጎ ውስጥ ተጀመረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኢትዮጵያ ለደረሰው የቦይንግ 737 ማክስ የአውሮፕላን አደጋ የካሳ ክስ ችሎት ቺካጎ ውስጥ ተጀመረ
በኢትዮጵያ ለደረሰው የቦይንግ 737 ማክስ የአውሮፕላን አደጋ የካሳ ክስ ችሎት ቺካጎ ውስጥ ተጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.11.2025
ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ ለደረሰው የቦይንግ 737 ማክስ የአውሮፕላን አደጋ የካሳ ክስ ችሎት ቺካጎ ውስጥ ተጀመረ

በጎሮጎሮሳውያኑ 2019 ከተከሰተው 157 መንገደኞች ከሞቱበት አደጋ ጋር በተያያዘ ሁለት የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች በትናንትናው ዕለት ለችሎት ቀርበዋል፤ ይህም ለተጎጂ ቤተሰቦች እና ወኪሎች ከስድስት ዓመት በላይ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በችሎት ውስጥ የመናገር እድል ሰጥቷቸዋል።

በአሜሪካ የሰሜን ኢሊኖይ ዲስትሪክት ፍርድ ቤት ከሚሰሙት አምስት ጉዳዮች መካከል የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ የተከፈቱት በአደጋው ሕይወታቸው ባለፈ የ28 ዓመቷ ኬንያዊት እና የ36 ዓመቷን ሕንዳዊት ቤተሰቦች ነው።

በርካታ የቤተሰብ አባላትን የሚወክለው ክሊፎርድ የሕግ ቢሮ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ፍርድ የሚሰጡ ከህዝብ የተወጣጡ ዳኞች ምርጫ እንደሚጀመርም ገልጿል።

ይህ ችሎት የቦይንግ ኩባንያ 1.1 ቢሊዮን ዶላር ክሳ በመክፈል የተጎጂዎቹ ቤተሰቦች የክስ አለመመስረት ስምምነት በመፈረም ክሱን አንዲተው ሞክሮ ባለመሳካቱ በድጋሚ ወደ ፍርድ ቤት መመለሱን በአሜሪካ ሚዲያዎች ተዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0