ሩሲያ ከቻይና እና ከሰሜን ኮሪያ ጋር በሚያዋስኗት ድንበሮች ላይ የሎጂስቲክስ ማዕከላትን ልታቋቁም ነው
17:32 04.11.2025 (የተሻሻለ: 17:34 04.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ ከቻይና እና ከሰሜን ኮሪያ ጋር በሚያዋስኗት ድንበሮች ላይ የሎጂስቲክስ ማዕከላትን ልታቋቁም ነው
ፕሬዝዳንት ፑቲን የመንግሥት አካላት የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ ማዕከላትን በየክልሉ እንዲያቋቁሙ መመሪያ ሰጥተዋል ሲል ክሬምሊን አስታውቋል።
ትኩረት የተሰጣቸው አካባቢዎች፦
🟠 ኒዥኔሊኒንስኮዬ-ቶንግጂያንግ የባቡር ድልድይ መሻገሪያ (የሩሲያዋን ኦብላስት ግዛት ከቻይናዋ ሄይሎንግጂያንግ ጋር የሚያገናኝ)
🟠 ብላጎቬሽቼንስክ-ሄይሄ የባቡር ድልድይ መሻገሪያ (የሩሲያዋን ብላጎቬሽቼንኮ ከተማ ከቻይናዋ ሄይሄ ከተማ ጋር ያገናኛል) እንዲሁም
🟠 በቱማናያ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው ድልድይ መሻገሪያ (ወደ ሰሜን ኮሪያ አቅጣጫ)
ፑቲን በተጨማሪም በሩቅ ምሥራቅና አርክቲክ ክልሎች እ.ኤ.አ. እስከ 2030 ድረስ የፋይናንስ ማዕከል እንዲቋቋም እና በትንሹ 10 የኢንዱስትሪና የቴክኖሎጂ ፓርኮች እንዲገነቡ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X