የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ'ኒውክለር ሪአክተር' የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሠራ ነው ተባለ
17:05 04.11.2025 (የተሻሻለ: 17:14 04.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ'ኒውክለር ሪአክተር' የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሠራ ነው ተባለ
በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት አብርሃም ደበበ (ዶ/ር)፣ የኒውክለር ጣቢያ ለመገንባት መታቀዱና የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን መቋቋም ዩኒቨርሲቲው እያከናወነ ላለው ተግባር ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ለአገር ውስጥ ሚዲያ አስረድተዋል።
ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ስምንት ዓመታት በዘርፉ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፦
▪ ዩኒቨርሲቲው ካሉት ስምንት የልህቀት ማዕከላት የኒውክለር ሪአክተር ቴክኖሎጂ አንዱ ነው።
▪ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን በማስተርስ መርሃ ግብር እያስተማረ ይገኛል።
▪ የዩኒቨርሲቲው የኒውክለር ሪአክተር ቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ሕንፃ ግንባታ ተጠናቅቋል።
▪ የላቦራቶሪ ዕቃዎችን ለማሟላት ከሚመለከተው አካል ጋር እየተሠራ ነው።
የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ተመስገን ወንድሙ (ዶ/ር)፣ በበኩላቸው “ዩኒቨርሲቲው ለኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን (በመቋቋም ላይ የሚገኘው) አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኑክሌር ልማት ፕሮጀክት ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X