አሜሪካ ጋዛ ውስጥ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ዓለም አቀፍ የደህንነት ኃይል እንዲቋቋም ሐሳብ አቀረበች

አሜሪካ ጋዛ ውስጥ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ዓለም አቀፍ የደህንነት ኃይል እንዲቋቋም ሐሳብ አቀረበች
አሜሪካ ያረቀቀችው የውሳኔ ሐሳብ፣ አሜሪካ እና ሌሎች ተሳታፊ አገራት እ.ኤ.አ እስከ 2027 መጨረሻ ድረስ ጋዛን እንዲያስተዳድሩ ሰፊ ሥልጣን የሚሰጥ ሲሆን፣ የአገልግሎት ዘመኑ ሊራዘምም ይችላል ሲል አክሲዮስ ዘግቧል።
በዘገባው መሠረት የሰነዱ ቁልፍ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦
ዓለም አቀፍ የደህንነት ኃይል (አይኤስኤፍ) የሰላም አስከባሪዎች ብቻ ሳይሆን አስገዳጅ ኃይልም ይሆናሉ።
የበርካታ አገራት ወታደሮች ተሳታፊ ሊሆኑ የሚችሉ ሲሆን፤ ይህ ዓለም አቀፍ ኃይል ትራምፕ የቦርዱ መሪ ሊሆኑ ከሚችሉበት “የሰላም ቦርድ” ጋር ተቀናጅቶ ይሠራል።
ወታደሮችን ለማዋጣት ፈቃደኛ የሆኑ አገራት ኢንዶኔዥያ፣ አዘርባጃን፣ ግብፅና ቱርክ መሆናቸው ተነግሯል።
የዓለም አቀፉ ኃይል ሥልጣን የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦ ድንበርን ማስጠበቅ፣ ሲቪሎችን መጠበቅ፣ ሰብዓዊ ኮሪደሮችን ማረጋገጥ፣ የፍልስጤም የፖሊስ ኃይልን ማሠልጠን፣ እና አስፈላጊ ከሆነ ሐማስን ትጥቅ ማስፈታትን ጨምሮ ጋዛን ከወታደራዊ ኃይል ነጻ ማድረግ።
ዓለም አቀፍ የደህንነት ኃይሉ ከእስራኤል እና ከግብፅ ጋር በመመካከር የሚንቀሳቀስ ሲሆን፤ ከዓለም አቀፍ ሕጎች ጋር የሚጣጣሙ "ሁሉንም አስፈላጊ እርምጃዎችን" ሊወስድ ይችላል።
የሰላም ቦርዱ የሽግግር አስተዳደርን፣ ለግንባታ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍን እና የጋዛን ሲቪል አስተዳደር የሚያስተዳድር የቴክኖክራት ፍልስጤማዊ ኮሚቴን ይቆጣጠራል።
ሰብአዊ ዕርዳታዎች የሚከፋፈሉት በተመድ እና በቀይ መስቀል በኩል ይሆናል።
ከውሳኔ ሐሳቡ ጋር የተያያዙ ውይይቶች በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት መካከል በቀጣይ ቀናት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ዓላማውም በቅርቡ ድምጽ ተሰጥቶበት የመጀመሪያው የጦር ኃይል በጥር ወር ወደ ጋዛ እንዲሰማራ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X