የተፈጥሮ ጥበቃ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ኅብረተሰቡን በባለቤትነት ማሳተፍ ይገባል - ደቡብ አፍሪካዊት የዘርፉ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የተፈጥሮ ጥበቃ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ኅብረተሰቡን በባለቤትነት ማሳተፍ ይገባል - ደቡብ አፍሪካዊት  የዘርፉ ባለሙያ

ደቡብ አፍሪካ በሰው እና በዱር እንስሳት መካከል የሚፈጠሩ የአኗኗር ተቃርኖዎችን የሚያስማሙ አሳታፊ ስልቶችን  በመተግበር፣ አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገቧን የአገሪቱ የደን፣ የዓሳ ሀብት እና የአካባቢ ጥበቃ መምሪያ የፕሮጀክት ማናጀር መርሴዲስ ማሬሌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"የእኔ ፕሮጀክት በደቡብ አፍሪካ ካለው የክሩገር ብሔራዊ ፓርክ ጎን ለጎን የሚተገበረው ነው። እናም በፓርኩ ዙሪያ ያሉት ማኀበረሰቦች በአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ላይ የመንግሥት እና ሕዝብ ዓይን እና ጆሮ ሆነው በንቃት እየሰሩ ነው።" ብለዋል።

መርሴዲስ ማሬሌ፣ የዱር እንስሳት ደህንነትን በማረጋገጥ የብሔራዊ ፓርኮችን የቱሪዝም አቅም ለማሳደግ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ማስፋት እንደሚገባም አመላክተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0