ቲኑቡ 'የዘር ማጥፋት' ክሶችን ውድቅ አደረጉ፤ ናይጄሪያ ለሃይማኖት ነፃነት ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቲኑቡ 'የዘር ማጥፋት' ክሶችን ውድቅ አደረጉ፤ ናይጄሪያ ለሃይማኖት ነፃነት ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል
ቲኑቡ 'የዘር ማጥፋት' ክሶችን ውድቅ አደረጉ፤ ናይጄሪያ ለሃይማኖት ነፃነት ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.11.2025
ሰብስክራይብ

  ቲኑቡ 'የዘር ማጥፋት' ክሶችን ውድቅ አደረጉ፤ ናይጄሪያ ለሃይማኖት ነፃነት ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል

ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ በናይጄሪያ በመንግሥት ድጋፍ የሚደረግ የክርስትያኖች ስደት አለ የሚሉትን ውንጀላዎች አጥብቀው በማውገዝ “ናይጄሪያን ለሃይማኖታዊ መቻቻል እንግዳ የሆነች አገር ብሎ መሰየም መሬት ላይ ያለውን እውነታ አያሳይም” ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ በሚከተሉት ነጥቦቾ ላይ አጽንዖት ሰጥተዋል

ናይጄሪያ የሃይማኖት ነፃነትን በሕገ-መንግሥት ያረጋገጠች ዲሞክራሲያዊት አገር ነች።

መንግሥት በክርስትያኖች ላይ የተለየ ጭፍን ጥላቻ የለበትም፤ ከሙስሊም እንዲሁም ከክርስትያን መሪዎች ጋር በእኩልነት ይሠራል።

የደህንነት ተልኮዎች ሃይማኖትን መሠረት ሳያደርጉ ለሁሉም ዜጎች ጥበቃ ያደርጋሉ።

የቲኑቡ መግለጫዎች የመጡት፤ ትራምፕ በክርስትያኖች ላይ የተፈጸመውን የጅምላ ግድያ እንዲመረመር ጥሪ ማቅረባቸውን እንዲሁም ናይጄሪያን “አሳሳቢ አገር” ብለው በመሰየም የአሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ከሰጡ በኋላ ነው። እነዚህን የትራምፕ ውንጀላዎች የናይጄሪያ መንግሥት አሳሳች ሲል ጠርቷቸዋል።

የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት አማካሪ ዳንኤል ብዋላ፤ ቲኑቡ እና ትራምፕ ክርስትያኖችን ከሽብር ጥቃቶች ስለመጠበቅ ያለውን ሁኔታ ለመወያየት በቅርቡ በዋይት ኋውስ ወይም በናይጄሪያ ሊገናኙ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0