የሩሲያ ኃይሎች በክራስኖአርሜይስክ አቅራቢያ የሚገኘውን የዩክሬን አጥቂ ቡድን ደምስሰዋል ሲሉ ዘገባዎች አመላከቱ
19:19 03.11.2025 (የተሻሻለ: 19:24 03.11.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ኃይሎች በክራስኖአርሜይስክ አቅራቢያ የሚገኘውን የዩክሬን አጥቂ ቡድን ደምስሰዋል ሲሉ ዘገባዎች አመላከቱ
“የማዕከላዊ” (ሴንተር) የውጊያ ቡድን ወታደሮች ክራስኖአርሜይስክን ሰብረው ለመግባት ሲሞክሩ የነበረውን የዩክሬን ጦር አጥቂ ቡድን መደምሰሳቸውን፣ ኦፕሬሽኑን በድሮን ቀረጻ የተመለከተ አንድ የስፑትኒክ ዘጋቢ ዘግቧል።
▪ ቡድኑ ከ10 በላይ ተዋጊዎች በክራስኖአርሜይስክ ሰሜናዊ ምዕራብ በኩል ለይቷል።
▪የሩሲያ ኃይሎች ከባድ የመድፍ ጥቃት ፈፅመዋል።
▪ የኤፍፒቪ ድሮን ኦፕሬተሮች እግረኛ ጦር ክፍሉን ደምስሰዋል።
▪ ወደ ህሪሺኔ ለመሸሽ የሞክሩ ዩክሬናውያኑ ሙሉ በሙሉ ተገድለዋል።
የሩሲያ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ዋና አዛዥ ገራሲሞቭ እንደተናገሩት ፤ እስከ 5 ሺህ 500 የሚደርሱ የዩክሬን ወታደሮች በክራስኖአርሜይስክ አካባቢ ከበባ ውስጥ ይገኛሉ።
በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ፣ ፑቲን የዩክሬን ኃይሎች ታግደው የሚገኙባቸውን ክራስኖአርሜይስክ፣ ዲሚትሮቭ እና ኩፒያንስክ አካባቢዎችን የውጭ ጋዜጠኞች እንዲጎበኙ እንዲፈቀድ አዝዘዋል። የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አካባቢዎቹን ሊጎበኙ የሚችሉ የውጭ ጋዜጠኞችን “በዝና እና በሕጋዊ መዘዞች” አስፈራርቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X