ኢትዮጵያ ስኬታማ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎችን እያከናወነች ነው - የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሺ ግርማ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ስኬታማ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎችን እያከናወነች ነው - የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሺ ግርማ

ሚኒስትር ዴኤታው፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቢሊየን የሚቆጠሩ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ፣  አገሪቱ በፖሊሲ የተደገፉ አበረታች የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን እያከናወነች መሆኗን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"የኢትዮጵያ የዱር አንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣንን ጨምሮ ጠንካራ ተቋማት አሉን። በተጨማሪም የአካባቢ ጥበቃ ጥረቶችን ማጠናከር የሚያስችሉ ተገቢ አሰራሮችም ተዘርግተዋል።" ብለዋል።

ክልሎች የደን ሽፋናቸውን እና የፓርኮቻቸውን ቁጥር ከማሳደግ አንፃር አበረታች እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ መሆኑንም ሰለሺ ግርማ አመላክተዋል።

የዓለም የዱር እንሰሳት ፕሮግራም ዓመታዊ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ ሲሆን በጉባኤው ከተለያዩ አገራት የተወጣጡ ፖሊሲ አውጪዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0