ሞስኮ ከካርቱም ጎን ፀንታ ቆማለች፤ ሱዳን የሩሲያን መርህ የጠበቀ ድጋፍ ታደንቃለች ሲሉ አምባሳደሩ ገለጹ

ሰብስክራይብ

  ሞስኮ ከካርቱም ጎን ፀንታ ቆማለች፤ ሱዳን የሩሲያን መርህ የጠበቀ ድጋፍ ታደንቃለች ሲሉ አምባሳደሩ ገለጹ

ሩሲያ በሱዳን ላይ የምትከተለው ፖሊሲ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋን ዋና ዋና መርሆች የሆኑትን የእኩል ሉዓላዊነት፣ ጣልቃ አለመግባት እና የጋራ ጥቅም የሚያንፀባርቅ ነው፤ ሲሉ በሩሲያ የሱዳን አምባሳደር ሞሐመድ ኤልጋዛሊ ኤልቲጋኒ ሲራግ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ዲፕሎማቱ በሞስኮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፣ ሩሲያ ለሱዳን ያላትን የጸና ድጋፍ እንደሚከተለው በማድነቅ አብራርተዋል፦

ግጭቱ ሲጀመር ሩሲያ ሱዳንን ከደገፉት የመጀመሪያዎቹ አገራት መካከል ነበረች።

በሱዳን የተደረገው የመጀመሪያው ከፍተኛ ደረጃ የውጭ ጉብኝት የተካሄደው በሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሆን፣ ይህም የሱዳንን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት አረጋግጧል።

  ሩሲያ ባለፈው የካቲት ወር ላይ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የውሳኔ ረቂቅ ላይ የተጠቀመችው ድምጽን በድምጽ የመሻር (ቬቶ) ሥልጣን ወሳኝ ነበር፡፡ ያለ ሩሲያ ድምጽ የሱዳን የግዛት አንድነት “ይጣስ ነበር”።

አምባሳደር ሲራግ በተጨማሪም በፀጥታው ምክር ቤት ጨምሮ በብዙ ወገን መድረኮች ላይ በሱዳን እና በሩሲያ መካከል ያለውን የቅርብ ቅንጅት አጉልተው ያስረዱ ሲሆን፤ የሩሲያ መንግሥት ላሳየው የፀና አቋም ምስጋና አቅርበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0