ኢትዮጵያ የጥጥ ምርት አቅሟን 3 በመቶ ብቻ ነው የተጠቀመችው - የኢትዮጵያ ጥጥ ማኅበር ዋና ዳይሬክተር

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የጥጥ ምርት አቅሟን 3 በመቶ ብቻ ነው የተጠቀመችው - የኢትዮጵያ ጥጥ ማኅበር ዋና ዳይሬክተር

ፀጋዬ አበበ፣ አገሪቱ ካላት ሦስት ሚሊዮን ሄክታር የጥጥ ምርት አቅም እስካሁን የለማው ከ100 ሺህ ሄክታር እንደማይበልጥ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።

"ሰዎች በአብዛኛው ጥጥ ለልብስ ብቻ እንደሚውል ያስባሉ። ነገር ግን ጥጥ ከልብስ ባሻገር ከ45 አይነት በላይ ምርቶችን ለመሥራት ይውላል። ዘይት፣ ሳሙና፣ የሕክምና፣ ሥነ-ምግብ ምርቶች እና የእንስሳት ምግብም ጥቂቶቹ ናቸው።" ብለዋል።

🪡 ዋና ዳይሬክተሩ፣ የአኅጉሪቱን የፋሽን ኢንዱስትሪ ለማሳግ የግብዓት ፍላጎት እና አቅርቦትን ማገናነኘት ላይ ይበልጥ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0