የምዕራባውያን ማዕቀቦች ቢኖሩም የሩሲያና ቻይና ግንኙነት እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲሉ የሩሲያው ጠቅላይ ሚኒስትር ገለጹ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየምዕራባውያን ማዕቀቦች ቢኖሩም የሩሲያና ቻይና ግንኙነት እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲሉ የሩሲያው ጠቅላይ ሚኒስትር ገለጹ
የምዕራባውያን ማዕቀቦች ቢኖሩም የሩሲያና ቻይና ግንኙነት እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲሉ የሩሲያው ጠቅላይ ሚኒስትር ገለጹ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.11.2025
ሰብስክራይብ

የምዕራባውያን ማዕቀቦች ቢኖሩም የሩሲያና ቻይና ግንኙነት እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲሉ የሩሲያው ጠቅላይ ሚኒስትር ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ሚሹስቲን በቻይና ሃንግዙ ከተማ ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር በሁለቱ አገራት የመንግሥት መሪዎች 30ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ውይይት፣ በአጋርነቱ ስትራቴጂያዊ ጥልቀት ላይ አጽንዖት ሰጥተዋል።

ሁለቱ መንግሥታት መሪዎቻቸው ያስቀመጧቸውን ለብዙ ዘርፍ ትብብር የሚሆኑ ሁሉንም ተግባራት በትጋት እየተገበሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ሚሹስቲን “በንግድ ልውውጦች ውስጥ የዶላር እና የዩሮ ድርሻ ወደ ስታትስቲካዊ ስህተት ደረጃ ወርዷል” ሲሉ የምዕራቡ የፋይናንስ ስርዓት መቀየሩን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ስትራቴጂካዊ ባህሪ ያገኙ ሰፊ የትብብር ዘርፎችን ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚከተለው ዘርዝረዋል ፦

🟠 ኢነርጂ፡ በነዳጅ፣ በጋዝ፣ በድንጋይ ከሰል እና በኒውክሌር ኃይል፤

🟠 ኢንዱስትሪ፡ አዳዲስ የጋራ ምርቶች እና የቴክኖሎጂ ጥምረቶች መፍጠር እና

🟠 ትራንስፖርት፡ የጭነት ልውውጥ ዕድገት እና የድንበር ተሻጋሪ መሠረተ-ልማት ግንባታ።

ሚሹስቲን በተጨማሪም አዲስ የኢንቨስትመንት ማስተዋወቅና የጋራ ጥበቃ ስምምነት ሕዳር 21 ሥራ ላይ እንደሚውል የገለጹ ሲሆን፤ ይህም አዳዲስ የጋራ አጋርነቶችን መፍጠርን እንደሚያበረታታ ይጠበቃል።

በምላሹም ሊ ኪያንግ በተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች መካከል የሁለቱንም አገራት ጥቅሞች በተሻለ ለመጠበቅ፣ ከሩሲያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የቻይናን ዝግጁነት አረጋግጠዋል። ሚሹስቲን የቻይና አቻቸውን ለመጪው የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ስብሰባ ሞስኮ እንዲገኙ ጋብዘዋቸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0