በ2018 በ4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ለመሥራት መታቀዱ ተዘገበ
16:59 03.11.2025 (የተሻሻለ: 17:04 03.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በ2018 በ4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ለመሥራት መታቀዱ ተዘገበ
የበጀት ዓመቱ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ በ21 ሺህ ተፋሰሶች ላይ እንደሚከናወን በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ሥራ አስፈጻሚ ፋኖሴ መኮንን ለአገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።
ሥራ አስፈፃሚው እንደተናገሩት፣ በተሠራው ሥራ የአፈር መሸርሸርን ቀንሷል፤ የደን ሽፋንን ጨምሯል፤ እንዲሁም የደረቁ የውሀ አካላት ተመልሰዋል፡፡
በየዓመቱ በአማካኝ 14 ሚሊዮን ህዝብ ተሳትፎ የሚያደርግበት ሲሆን፣ በዓመትም እንደክልሎች ተጨባጭ ሁኔታ ከ30 እስከ 60 ቀን የሚቆይ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራ እንደሚከናውን ጠቁመዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X