ኢትዮጵያ የደቡባዊ ዓለም አገራት የዱር እንስሳት ሀብቶቻቸውን ለመጠበቅ እና ለማስተዋወቅ በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቀረበች
16:04 03.11.2025 (የተሻሻለ: 16:14 03.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የደቡባዊ ዓለም አገራት የዱር እንስሳት ሀብቶቻቸውን ለመጠበቅ እና ለማስተዋወቅ በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቀረበች
የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ ሰለሺ ግርማ፣ በፋይናንስ እና ሌሎች ችግሮች ምክንያት እድሉ ያላገኙ በተለይም የደቡባዊ ዓለም አገራት እንዲተባበሩ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም የዱር እንሰሳት ፕሮግራም ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ጥሪ ማቅረባቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል፡፡
በኢትዮጵያ ለቱሪዝምና ለዱር እንሰሳት ጥበቃ ያለውን ምቹ ምህዳር በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ገልፀዋል።
የአገሪቱ የዱር እንስሳት ጥበቃ ተልዕኮ “የዱር እንስሳት ኃብቶችን መጠበቅና ሳይንስን መሠረት ባደረገ ማኅበረሰብ-መር አያያዞች በዘላቂነት መጠቀም ነው “ ሲሉ አስረድተዋል፡፡
በጉባኤው ከአፍሪካ፣ ከላቲን አሜሪካ፣ ከእስያ እና ከካሪቢያን የተውጣጡ ከ30 በላይ አገራት የመንግሥት ባለሥልጣናት እና ባለሙያዎች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

