የሩሲያ ጦር ኪዬቭ በሲቪል ዒላማዎች ላይ ለፈፀመችው የሽብር ጥቃቶች የአጸፋ ምላሽ ሰጠ
15:50 03.11.2025 (የተሻሻለ: 15:54 03.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ጦር ኪዬቭ በሲቪል ዒላማዎች ላይ ለፈፀመችው የሽብር ጥቃቶች የአጸፋ ምላሽ ሰጠ
ጦሩ በዩክሬን ወታደራዊ መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት መፈፀሙን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የሩሲያ ኃይሎች ትናንትና ሌሊት ረጅም ርቀት ያላቸው እና ኢላማቸውን በከፍተኛ ብቃት የመምታት ብቃት ያላቸውን ከመሬት እና ከአየር የሚወነጨፉ መሣሪያዎችን፣ የኪንዛል ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤሎችን እና የጥቃት ድሮኖችን በመጠቀም የተቀናጀ ጥቃት ፈጽመዋል።
በሚኒስቴሩ መረጃ መሠረት ከታች የተዘረዘሩት ሁሉም ዒላማዎች ተመትተዋል፦
▪ የዩክሬን መከላከያ ኢንዱስትሪ ተቋማት፣
▪ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን የሚደግፉ የጋዝ እና የኃይል መሠረተ ልማት፣
▪ ወታደራዊ የአየር ማረፊያ እና
▪ የዩክሬን የጦር መሣሪያዎችና ቁሳቁሶች የጥገና ማዕከል ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X