በ2018 60 ሚሊዮን ዜጎችን በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ መታቀዱ ተዘገበ
15:25 03.11.2025 (የተሻሻለ: 15:34 03.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በ2018 60 ሚሊዮን ዜጎችን በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ መታቀዱ ተዘገበ
እስካሁን ከ27 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መመዝገባቸውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የምዝገባ አስተባባሪ ደጀኔ ገብሬ ለአገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
🪪 ለሁሉም ነዋሪዎች መታወቂያውን በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ ሰፋፊ ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን፦
◻ በአሁኑ ወቅት ከ5,000 በላይ የመመዝገቢያ ማሽኖች አገልግሎት ላይ ናቸው፡፡
◻ እስከ በጀት ዓመቱ አጋማሽ ድረስ የማሽኖቹን ቁጥር ወደ 10, 000 በማሳደግ ተደራሽነትን ለማስፋት ታቅዷል።
◻ በዓመቱ የታቀደውን የ60 ሚሊዮን ዜጎች ምዝገባ ለማሳካት ጠንካራ ርብርብ እየተደረገ ነው።
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ወደ ሩቅ አካባቢዎች እንዲደርስ በተንቀሳቃሽ የምዝገባ ጣቢያዎች (Mobile Registration Units) አማካኝነት እየተሰራ መሆኑን አስተባባሪው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X