ዋሽንግተን ወታደሮቿን ወደ ናይጄሪያ የመላክ ሐሳቧን አልቀየረችም ሲሉ ትራምፕ ተናገሩ
13:44 03.11.2025 (የተሻሻለ: 13:54 03.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዋሽንግተን ወታደሮቿን ወደ ናይጄሪያ የመላክ ሐሳቧን አልቀየረችም ሲሉ ትራምፕ ተናገሩ
ትራምፕ በ'ኤር ፎርስ ዋን' አውሮፕላን ውስጥ ሆነው ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "ሊሆን ይችላል... ብዙ ነገሮችን እያሰብኩ ነው። በናይጄሪያ የክርስቲያኖችን ግድያ በክብረወሰን ደረጃ ከፍተኛ ነው፡፡"
ቅዳሜ ዕለት ፕሬዝዳንቱ “እስላማዊ አሸባሪዎችን ለማጥፋት” በአፍሪካዊቷ አገር ላይ ለሚደረግ ጥቃት ፔንታጎን እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ እንደሚሰጡ ተናግረዋል። የክርስቲያኖች ግድያ ከቀጠለ አሜሪካ ለናይጄሪያ የምትሰጠውን ሁሉንም ዕርዳታ በአስቸኳይ እንደምታቆምም አክለዋል።
ከዚህ ቀደም የፔንታጎን ዋና ኃላፊ ፒት ሄግሴት መምሪያቸው በትራምፕ ትዕዛዝ መሠረት በናይጄሪያ ላይ ለሚወሰድ እርምጃ እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።
በናይጄሪያ የክርስቲያኖች የዘር ማጥፋት ወንጀል ውንጀላ አስመልክቶ፣ አቡጃ የአገሪቱን የደህንነት ችግሮች ተቀብላለች፡፡ ነገር ግን ክርስቲያኖች በተለየ ሁኔታ ዒላማ እየተደረጉ እንዳልሆነ አስረድታ፣ የደህንነት ተግዳሮቶችን ለማስወገድ የሚካሄደውን ትግል አክብሮት እንዲሰጠው ጥሪ አቅርባለችል።
የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው፣ ፕሬዝደንት ቦላ ቲኑቡ እና ትራምፕ ክርስቲያኖችን ከአሸባሪዎች ጥቃት በመጠበቅ ዙሪያ ለመወያየት በሚቀጥለው ሳምንት በዋይት ኋውስ ወይም በናይጄሪያ ሊገናኙ ይችላሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X