የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ጥቃት 5ኛ ዓመትን እየዘከረ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ጥቃት 5ኛ ዓመትን እየዘከረ ነው
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ጥቃት 5ኛ ዓመትን እየዘከረ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.11.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ጥቃት 5ኛ ዓመትን እየዘከረ ነው

ከአምስት ዓመት በፊት 24/2013 ዓ.ም ትግራይ ክልል ውስጥ በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመው ጥቃት "እንዳይደገም፤ መቼም አንረሳውም" በሚል መሪ ቃል በሠራዊቱ እየታሰበ ይገኛል፡፡

ማዕከላዊ ዕዝ በትናንትናው ዕለት ሻማ በማብራት ሥነ-ሥርዓት ጥቃቱን አስቦ አምሽቷል፡፡

የሠራዊት አባላቱ "ክስተቱ እንዳይደገም የምናስብበት እና የተሠዉትን ሰማዕታትን የምናስታውስበት ቀን ነው" ማለታቸውን መከላከያ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አስታውቋል።

የሰሜን ዕዝ ጥቃት የሰሜኑ ጦርነት መንሳኤ እንደሆነ በኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ የተገለፀ ሲሆን ሕወሓት ክሱን አስተባብሏል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት የሰላም ስምምነት ተፈራርመው ጦርነቱ ቆሟል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ጥቃት 5ኛ ዓመትን እየዘከረ ነው
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ጥቃት 5ኛ ዓመትን እየዘከረ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.11.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0