የእስራኤል ጦር በኻን ዩኒስ በፈፀማቸው የአየር ጥቃቶች የሕክምና አቅርቦት ተቋርጧል፣ አካባቢውም በፍርስራሽ ክምር ተሞልቷል

ሰብስክራይብ

የእስራኤል ጦር በኻን ዩኒስ በፈፀማቸው የአየር ጥቃቶች የሕክምና አቅርቦት ተቋርጧል፣ አካባቢውም በፍርስራሽ ክምር ተሞልቷል

በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያሉ የቅርብ ጊዜ ክንውኖች፦

በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ የሚገኘው የኻን ዩኒስ ምስራቃዊ ክፍል ትናትና ጠዋት በእስራኤል የአየር ጥቃት እንደተፈፀመበት የፍልስጤም መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ሁኔታው አስቸኳይ ቢሆንም እስራኤል የመድኃኒትና የሕክምና አቅርቦቶችን እንዲገባ መከልከሏን ቀጥላለች ሲሉ የጋዛ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ገልፀዋል።

የአል-ሺፋ ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር ሙሐመድ አቡ ሰልሚያ እንደተናገሩት፤፣ ሁለት ሺህ ሕፃናትን ጨምሮ ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ እጅና እግራቸውን ያጡ ሰዎች አፋጣኝ የሰው ሠራሽ አካላት ሕክምና ያስፈልጋቸዋል።

የማዘጋጃ ቤቱ ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው፣ ወደ 260 ሺህ ቶን የሚጠጋ ፍርስራሽ (ቆሻሻ) በጋዛ ጎዳናዎች እና የቆሻሻ መጣያ ቦታዎች ላይ ተከምሯል።

የአካባቢው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ የመስከረም 30 የተኩስ አቁም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ በእስራኤል የጥቃት እርምጃ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ 226 ሰዎች ተገድለው 594 ቆስለዋል።

ቅዳሜ ዕለት የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ አባላት ኢስታንቡል ውስጥ ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳንን የተገናኙ  ሲሆን፣ በጋዛ የተኩስ አቁም ሁኔታ እና አስቸኳይ ሰብአዊ ፍላጎቶች ላይ ተወያይተዋል።

በቪዲዮው በእስራኤል ጦር ተደጋጋሚ የቦምብ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ በጋዛ የቀሩ ፍርስራሾች ያሳያል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0