የሩሲያ ልዕለ ኃያሉ መሣሪያ 'ፖሳይደን' በምዕራቡ ዓለም እንደ ማስፈራሪያነት ይፋ ሆኗል - ሚዲያ
20:02 02.11.2025 (የተሻሻለ: 20:14 02.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ልዕለ ኃያሉ መሣሪያ 'ፖሳይደን' በምዕራቡ ዓለም እንደ ማስፈራሪያነት ይፋ ሆኗል - ሚዲያ
ፖሳይደን የተነደፈው በውሃ ውስጥ ሳይታወቅ ለመጓዝ እና ለባሕር ዳርቻ ወሳኝ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ለማድረግ መሆኑን የምዕራባያን ሚዲያ ዘግቧል፡፡
በኒውክሌር ኃይል የሚሠራው ይህ ጦር መሣሪያ የሚከተሉት ይዘቶች እንዳሉት ተዘግቧል፦
በውሃ ውስጥ የመሰወር ችሎታ አለው።
ወደቦች እና የባሕር ኃይል ጣቢያዎችን የማውደም አቅም አለው።
የኒውክሌር ማሽከርከሪያ/ማስወንጨፊያ ያለው ሲሆን፣ የባሕር ሰርጓጅ መርከብ እና የቶርፔዶ ባህሪያትን አጣምሮ ይዟል።
በሩሲያ ባሕር ኃይል ትንተና ማዕከል የወታደራዊ ጥናት መርሃ ግብር ተመራማሪ የሆኑት ሚካኤል ቢ. ፒተርሰን እንደተናገሩት፣ “ከጦርነት ተግባር ይልቅ፣ አስገዳጅ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ተቃዋሚ ኃይል ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ ለማስገደድ እንደ ማስፈራሪያ ለመጠቀም ነው የተነደፈው፡፡”
ጥቅምት 19 ቭላድሚር ፑቲን የፖሳይደን የተሳካ ሙከራ መደረጉን አስታውቀው፣ "እንደሱ ያለ ምንም የለም፤ እናም በቅርብ ጊዜ ውስጥም አይኖርም" ሲሉ መግለፃቸው ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/