በማዳጋስካር ሊካሄድ የነበረው የምስራቅ አፍሪካ የካራቴ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ሊደርገ ነው
19:36 02.11.2025 (የተሻሻለ: 19:54 02.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በማዳጋስካር ሊካሄድ የነበረው የምስራቅ አፍሪካ የካራቴ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ሊደርገ ነው
በአገሪቱ "ወቅታዊ የፀጥታ ችግር ምክንያት ኢትዮጵያ እንድታዘጋጅ በፌዴሬሽኑ ጥረት መሳካቱን" የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሙሉነህ ጎሳዬ ገልፀዋል።
ከታህሳስ 13 እስከ 15 ፥ 2018 ዓ.ም በሚካሄደው ሻምፒዮና 14 አገራት እንደሚሳተፉ ማረጋገጫ የሰጡ ሲሆኑ፤ ኢትዮጵያ በተለያዩ ምድቦች መሳተፍ እንድትችል እድል የሰጠ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
የካራቴ ሻምፒዮናው ከውድድር ባሻገር የአሠልጣኞች ሥልጠና እና የዳኝነት ሥልጠና የሚሰጥ እንደሆነም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል።
የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን 15ኛውን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የክልልና ከተማ አስተዳደር የጉባኤው አባላት በተገኙበት በትናትናው ዕለት መካሄዱንም የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X