በዲጂታል ክፍያ ከ17 ትሪሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር ሲፈፀም በሞባይል ባንኪንግ 76% በላይ ድርሻ መያዙ ተዘገበ
18:19 02.11.2025 (የተሻሻለ: 18:24 02.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በዲጂታል ክፍያ ከ17 ትሪሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር ሲፈፀም በሞባይል ባንኪንግ 76% በላይ ድርሻ መያዙ ተዘገበ
በ2017 የበጀት ዓመት አፈጻጸም ከቀዳሚው ዓመት በእጥፍ እንደሚበልጥ ተጠቁሟል።
በ2016 በሞባይል ባንኪንግ የተንቀሳቀሰው 6.71 ትሪሊዮን ብር በ2017 ወደ ከ13.1 ትሪሊዮን ብር አድጓል፡፡
ሚዲያው ኢት-ስዊች አክሲዮን ማኅበርን ዋቢ አድርጎ በበጀት ዓመቱ ዋና ዋና ያላቸውን የዲጂታል ገንዘብ ግኝቶች እንደሚከተለው አጋርቷል፦
በሞባይል ዋሌት አማካኝነት 2.08 ትሪሊዮን ብር የገንዘብ ዝውውር ተደርጓል (የእጥፍ ጭማሪ አለው)።
በኢንተርኔት አማካኝነት 1.7 ትሪሊዮን ብር ተንቀሳቅሷል።
በኤትኤም 729.8 ቢሊዮን ብር ሲንቀሳቀስ ካለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር ብዙ ዕደገት አላሳየም።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መረጃን ዋቢ ያደረገው የአገር ውስጥ የግል ሚዲያ፣ የሞባይል ባንክ የገንዘብ ዝውውር ከኤትኤምና ከፖስ (PoS) አንጻር ከፍተኛ ደረጃ ዕድገት እያሳየ ነው ብሏል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X