አሜሪካ በካሪቢያን ባሕር አንድ መርከብ ላይ በፈፀመችው ጥቃት ሦስት 'አደንዛዥ ዕፅ አሸባሪዎች' ተገደሉ
17:53 02.11.2025 (የተሻሻለ: 17:54 02.11.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አሜሪካ በካሪቢያን ባሕር አንድ መርከብ ላይ በፈፀመችው ጥቃት ሦስት 'አደንዛዥ ዕፅ አሸባሪዎች' ተገደሉ
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ እንዳስሳወቁት፣ አደንዛዥ ዕፅ እንደጫነች በተጠረጠረች መርከብ ላይ "ገዳይ የሆነ ከፍተኛ ጥቃት" ተፈጽሟል።
"ይህች መርከብ ልክ እንደሌሎች ሁሉ በእኛ መረጃ ሕገ-ወጥ ዕፅ ዝውውር ውስጥ እንደምትሳተፍ፣ በታወቀው የዕፅ አዘዋዋሪዎች መስመር ላይ እንደምትጓዝ እና አደንዛዥ ዕፅ እንደያዘች ይታወቅ ነበር" ብለዋል።
ሄግሴት የአሜሪካ መሥሪያ ቤታቸው "ይከታተላቸዋል (የዕፅ አዘዋዋሪዎችን )፤ ጠምዳቸዋል፤ ያድናቸዋል እናም ይገድላቸዋል፡፡" ሲሉ ቃል ገብተዋል።
ይህ ዘመቻ ባለፉት ሁለት ወራት ዋሽንግተን በፓሲፊክ እና በካሪቢያን ባሕር በኩል በአደንዛዥ ዕፅ መግቢያ ላይ ያደረገቻቸው የሞት አደጋ ያስከተሉ ተከታታይ ጥቃቶች አካል ነው።
የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት አገራቸው ባለፉት 100 ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋውን የአሜሪካ ወረራ ስጋት እንደገጠማት በተደጋጋሚ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X