ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ እንድታሸንፍ የሚያደርጋትን የእግር ኳስ ቡድን እያዘጋጀች መሆኑ ተዘገበ
15:18 02.11.2025 (የተሻሻለ: 15:24 02.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ እንድታሸንፍ የሚያደርጋትን የእግር ኳስ ቡድን እያዘጋጀች መሆኑ ተዘገበ
"ሮድ ቱ 2029" (Road to 2029) በተሰኘው ፕሮጀክት አገሪቱ ለማስተናገድ ያሰበችውን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ባለድል የሚያደርጋትን የታዳጊዎች ስብስብ መመልመሏን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ባሕሩ ጥላሁን ለአገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ "ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች የተውጣጡ 85 ታዳጊዎች ለዘጠኝ ወራት ሥልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው 26ቱ ተመርጠው የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ሥልጠና እየወሰዱ ነው" ብለዋል።
"ሮድ ቱ 2029" በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሠልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ መሆኑን የገለጹት ባሕሩ ጥላሁን፣ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ዘገባው፣ ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በመጭው ኅዳር በምታስተናግደው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማኅበር ምክር ቤት ዞን ይሳተፋሉ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


