የታንዛኒያ ተቃዋሚዎች ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሐሰን ምርጫውን በዝረራ ማሸነፋቸውን ውድቅ አደረጉ
12:29 02.11.2025 (የተሻሻለ: 12:34 02.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የታንዛኒያ ተቃዋሚዎች ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሐሰን ምርጫውን በዝረራ ማሸነፋቸውን ውድቅ አደረጉ
ምርጫው ቁልፍ ተወዳዳሪዎች ያገለለ መሆኑን እና በድህረ ምርጫውን የተከሰተውን ደም አፋሳሽ ተቃውሞዎችን እንደ ምክንያት ጠቅሰዋል።
የሀገሪቱ ዋንኛ ተቃዋሚ ቻዴማ (CHADEMA) በምርጫው እንዳይሳተፍ የተከለከለው የሥነ-ምግባር ደንብ ተቀብሎ ባለመፈረሙ ሲሆን የፓርቲው መሪ ቱንዱ ሊሱ ባለፈው ሚያዝያ ወር በአገር ክህደት ተይዘው ነበር። “ሙሉ በሙሉ የፈጠራ ውጤት” ሲሉ በትናንት ዕለት ገልፀዋል።
ትክክለኛ ምርጫ አልተካሄደም እንዲሁም በመላ አገሪቱ የተካሄዱት ሰልፎች ዜጎች የተበላሸውን የምርጫ ሂደት እና ውጤቱን እንደማይቀበሉ አረጋግጠዋል ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ ጽፈዋል፡፡
በተቃራኒው የምርጫ ኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሐሰን 97.66% ድምፅ (ከ31.9 ሚሊዮን በላይ) ማግኘታቸውን፣ የመራጮች ተሳትፎ ደግሞ ወደ 87% መድረሱን አስታውቋል።
የደህንነት ኃይሎች ከመጠን ያለፈ እርምጃ አልወሰዱም ሲሉ የታንዛኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሕሙድ ታቢት ተናግረዋል። በሰልፉ ወቅት የተከሰተውን ረብሻ አስመልክተው “እጅግ በጣም ጥቂት የሆኑ አነስተኛ ክስተቶች” ሲሉ ሁኔታውን አቃልለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X