በ2025 የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያቀኑ የሩሲያ ቱሪስቶች ቁጥር በ28.5 በመቶ ጨመረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበ2025 የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያቀኑ የሩሲያ ቱሪስቶች ቁጥር በ28
በ2025 የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያቀኑ የሩሲያ ቱሪስቶች ቁጥር በ28 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.11.2025
ሰብስክራይብ

በ2025 የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያቀኑ የሩሲያ ቱሪስቶች ቁጥር በ28.5 በመቶ ጨመረ

የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ስታቲስቲክስ አገልግሎት እንደዘገበው፣ ከጥር ወር ጀምሮ 25,267 የሩሲያ ዜጎች ሀገሪቱን የጎበኙ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ በ2024 በተመሳሳይ ወቅት ከነበሩት 19,661 ጎብኝዎች ጋር ሲነጻጸር ጭማሪ አሳይቷል።

ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ ባሳለፍነው የመስከረም ወር፦

🟠 ከ1,500 በላይ ሩሲያውያን ኬፕ ታውን አየር ማረፊያ ደርሰዋል::

🟠ወደ 1,200 የሚጠጉት በጆሃንስበርግ አየር ማረፊያ አቀባበል ተደርጎላቸዋል::

🟠134 የሩሲያ ቱሪስቶች በየብስ መንገድ ተጉዘው ሄደዋል።

ወደ አገሪቱ ካቀኑት መካከል፣ 2,840 ለረፍት ጉዞ፣ 53 ለንግድ እና 6 ለትምህርት የተጓዙ ናቸው።

ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካ ከቪዛ ነፃ የጉዞ ስምምነት ያላቸው ሲሆን በ2017 መንግሥት ሀገሪቱን የሚጎበኙ የውጭ ቱሪስቶችን ለመጠበቅ ተጨማሪ የደህንነት እርምጃዎችን ማስተዋወቁን የደቡብ አፍሪካ ሚዲያ ዘግቧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0