ትራምፕ ክርስትያኖች እየተሰደዱ ነው በሚል ክስ ናይጄሪያን 'ልዩ ስጋት ያለባት ሀገር' ብለው ፈረጁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱትራምፕ ክርስትያኖች እየተሰደዱ ነው በሚል ክስ ናይጄሪያን 'ልዩ ስጋት ያለባት ሀገር' ብለው ፈረጁ
ትራምፕ ክርስትያኖች እየተሰደዱ ነው በሚል ክስ ናይጄሪያን 'ልዩ ስጋት ያለባት ሀገር' ብለው ፈረጁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.11.2025
ሰብስክራይብ

ትራምፕ ክርስትያኖች እየተሰደዱ ነው በሚል ክስ ናይጄሪያን 'ልዩ ስጋት ያለባት ሀገር' ብለው ፈረጁ

ይህ ውሳኔ የመጣው በአሜሪካና በአውሮፓ ያሉ ወግ አጥባቂ ግለሰቦች በናይጄሪያ የክርስትያኖች የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመ ነው የሚል ክስ በዘመቻ ካቀረቡ በኋላ ነው።

ትራምፕ ራሳቸው ሁኔታውን ለማሻሻል ትኩረት እንደሰጡ ገልጸው፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ክርስትያኖች በ"ጽንፈኛ እስላማውያን" ተገድለዋልና ክርስትና የሕልውና አደጋ እንደገጠመው አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል፣ የናይጄሪያ መንግሥት የሀገሪቱን የጸጥታ ችግሮች እውቅና ቢሰጥም፣ ክርስትያኖች በተለየ መልኩ ዒላማ እንዳልሆኑ ገልጿል። መንግሥት ችግሮቹ እየተፈቱ መሆናቸውንም አክሏል።

የመረጃ ሚኒስትር ሞሐመድ ኢድሪስ ናይጄሪያ ሁሉንም አይነት የጸጥታ ችግሮች በጋራ የምትዋጋ፤ የብዝኃ ሐይማኖቶች ሀገር እንደሆነች መረዳት እና ማክበር እንደሚገባ አሳስበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0