ባለፉት ሦስት ወራት በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ 10 ፋብሪካዎች ሥራ ጀምረዋል ተባለ
18:45 01.11.2025 (የተሻሻለ: 18:54 01.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ባለፉት ሦስት ወራት በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ 10 ፋብሪካዎች ሥራ ጀምረዋል ተባለ
ፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ በፓርኮቹ ተጨማሪ 31 ፋብሪካዎች በቅርቡ ሥራ ለመጀመር የሚያስችላቸውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል።
ከኢንዱስትሪ ፓርኮች በወጪ ንግድ 47 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘት መቻሉን መናገራቸውንም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አስነብቧል፡፡
በፓርኮቹ 6 ማኅበራት እና 67 የሕብረት ሥራ ማኅበራትን ጨምሮ በአጠቃይ 272 ሺህ 635 አርሶ አደሮች በግብዓት ትስስር ፈጥረዋል ነው የተባለው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X