በዘንድሮው ዓመት 20.77 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበዘንድሮው ዓመት 20
በዘንድሮው ዓመት 20 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.11.2025
ሰብስክራይብ

በዘንድሮው ዓመት 20.77 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

ቀድሞ 20.41 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን የተያዘውን ዓመታዊ ዕቅድ በተሻለ አፈፃፀም ማሳካት መቻሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

በሚኒስቴሩ የሰብል ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢሳያስ ለማ፣ በአጠቃላይ ከታረሰው መሬት ውስጥ 60 በመቶ ያህሉ "በክላስተር እርሻ" መከናወኑ ለውጤቱ አስተዋፅኦ ማድረጉን ለአገር ውስጥ ሚዲያ ገልፀዋል።

ይህም ሀገሪቱ በ2018 የምርት ዘመን 653 ሚሊዮን ኩንታል ለመሰብሰብ ያስቀመጠችውን ግብ ለማሳካት ወሳኝ እርምጃ ነው ብለዋል።

የሚጠበቀውን ያህል ምርቱ ለማግኘት ሜካናይዜሽንን የማስፋፋት፣ ቀድመው የሚደርሱ የሰብል ዝርያዎችን የመጠቀም እና ለገበሬዎች ወሳኝ የግብርና መረጃዎችን የማቅረብ ጥረቶች መከናወናቸውም ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0