ሩሲያ የተባበሩት መንግሥታት የሊቢያ ድጋፍ ተልዕኮ የሥልጣን ዘመን ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለማራዘም በእንግሊዝ የተዘጋጀውን ረቂቅ ውሳኔ እንደምትደግፍ ገለፀች
14:49 01.11.2025 (የተሻሻለ: 14:54 01.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ የተባበሩት መንግሥታት የሊቢያ ድጋፍ ተልዕኮ የሥልጣን ዘመን ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለማራዘም በእንግሊዝ የተዘጋጀውን ረቂቅ ውሳኔ እንደምትደግፍ ገለፀች
"ተልዕኮው በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ዓለም አቀፍ የሽምግልና ጥረቶች ማዕከላዊ ሚና መጫወቱን ቀጥሏል ብለን እናምናለን፣ እናም በሀገር ውስጥ ያለው ተለዕኮና በዚያ መገኘት ሁኔታው ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲረጋጋ አስፈላጊ ነው" ሲሉ የሩሲያ ቋሚ ተወካይ ቫሲሊ ኔበንዚያ ተናግረዋል፡፡
ሰነዱ የተባበሩት መንግሥታት የሊቢያ ድጋፍ ተልዕኮ አሁን ባለው ሁኔታ ሥራውን ለማነቃቃት ቁልፍ የዋና ጸሐፊውን ምክሮች ማካተቱን በመጥቀስ፣ በድርድሩ ወቅት የጸሐፊዎቹን ገንቢ አቋም አጉልቶ አሳይቷል ብለዋል።
ኔበንዚያ የተልዕኮው የሥልጣን ዘመን የሚከተሉትን ማድረግ እንዳለበት በዝርዝር አስቀምጠዋል፦
🟠 ለሊቢያ ግጭት የፖለቲካ መፍትሔ ቅድሚያ መስጠት፣
🟠በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን ተሳትፎ ማስፋፋት (ቤንጋዚ እና ሰብሃን ጨምሮ)፣
🟠በተለይም የበርሊን ሂደትን በመጠቀም ሁሉንም አባላቱን በማሳተፍ የውጭ ድጋፍን ማነቃቃት፡፡
"በሊቢያ ያለው የሽግግር ወቅት ከልክ በላይ መራዘሙ ግልጽ ነው። አሁን ያለው አለመረጋጋት በጨመረ ቁጥር ሀገሪቱን አጣብቂኝ ውስ የሚከቱ ችግሮች ይበልጥ እየተስፋፉ ይሄዳሉ። የተልዕኮው ዘመነ ሥልጣን በሊቢያውያን መካከል ያለውን ውይይት በመደገፍ ውጤታማነቱን እንደሚያሳድግ ተስፋ ይደረጋል።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X