ኢትዮጵያ ቀይ ባሕርን ያጣችበት መንገድ ተፈጥሯዊ ሳይሆን ሰው ሠራሽ ነው - ተንታኝ
21:36 31.10.2025 (የተሻሻለ: 21:44 31.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ቀይ ባሕርን ያጣችበት መንገድ ተፈጥሯዊ ሳይሆን ሰው ሠራሽ ነው - ተንታኝ
ሀገሪቱ የተባበሩት መንግሥታት የባሕር ሕግ ስምምነትን በመጥቀስ በሕጋዊ መንገድ ብሎም በታሪክ ሚዛን የባሕር በር የማግኘት መብት አላት ሲሉ በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ መምህር ደረጄ ኃይሌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ቀጣናውን ከመካረር በትብብር ለማሳደግ ድርድር እና ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ቀዳሚው አማራጭ መሆን እንዳለበት ያነሱት መምህር ደረጄ፤ በዚህ ረገድ ሩሲያ ገለልተኛ አሸማጋይ ሆና መቅረብ እንደምትችል አስረድተዋል፡፡
"ኢትዮጵያም ኤርትራም የራሳቸው ፍላጎት ሊኖራቸው ይችላል፤ ይህን ግን ወደ ጋራ ልማት መቀየር ይጠበቅባቸዋል" ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ እና አስመራ የተረጋጋ እና በኢኮኖሚ የተሳሰረ ግንኙነት መመስረት ከቻሉ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደህነነት ማምጣት ይቻላል ሲሉም አመላክተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X