ሩሲያ በሱዳን ትይዩ የሥልጣን መዋቅር መፈጠሩን አትቀበልም - በተባበሩት መንግሥታት የሩሲያ አምባሳደር
20:14 31.10.2025 (የተሻሻለ: 20:24 31.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ በሱዳን ትይዩ የሥልጣን መዋቅር መፈጠሩን አትቀበልም - በተባበሩት መንግሥታት የሩሲያ አምባሳደር
ይህ እርምጃ በሞስኮ እና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ውድቅ የተደረገ እና ለሰላም እንቅፋት እንደሆነ ይቆጠራል ሲሉ ቫሲሊ ኔቤንዝያ ጥቅምት 20 በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ አብራርተዋል።
ሞስኮ በሱዳን ያለው ሁኔታ በጥልቅ ያሳስባታል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ኔቤንዝያ በተለይ አል-ፋሸር በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ስለመያዙ እና የተፈጸሙ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ጠቅሰዋል።
ሩሲያ የሱዳንን የዘር ግጭት በጽኑ ታወግዛለች ሲሉም አክለዋል።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ የሚደረጉ ጥረቶችን ሲያስተጓጎል፤ የሱዳን መንግሥት ግን ለቅንጅት እና ውጤታማ የእርዳታ ስርጭት ዝግጁ እንደሆነ አምባሳደሩ አንስተዋል።
ሞስኮ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እና በራሳቸው በሱዳናውያን ተመርቶ፤ የሀገሪቱን አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የሚያረጋግጥ የፖለቲካ ሂደት እንዲፈጠር ታበረታታለች ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X