የኢትዮጵያውያን አርቲስቶች የስዕል እና የቅርጻ ቅርጽ አውደ ርዕይ በሩሲያ የሳይንስ እና ባሕል ማዕከል ተከፈተ
19:46 31.10.2025 (የተሻሻለ: 19:54 31.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያውያን አርቲስቶች የስዕል እና የቅርጻ ቅርጽ አውደ ርዕይ በሩሲያ የሳይንስ እና ባሕል ማዕከል ተከፈተ
ተስፋዬ ጋሼ፣ ጸጋጽዮን ክፍሌ፣ ተስፋሁን ክብሩ እና አማን ባደግ ከሌሎች የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎች ጋር የሚያቀርቡት የሥነ-ጥበብ ሥራ፤ በፑሽኪን አዳራሽ ለአንድ ሳምንት ለሕዝብ እይታ ክፍት እንደሚሆን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል፡፡
ኤግዚቢሽኑን በንግግር የከፈቱት በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ይቭጌኒ ተረኺን፤ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በባሕል ትስስር፣ በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እና በሌሎች በርካታ መስኮች እያደገ መምጣቱን ገልጸው፤ መሰል ዝግጅቶች ግንኙነቱን ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል።
የሩሲያ የሳይንስ እና የባሕል ማዕከል በሁለቱ ሀገራት እና ሕዝቦች መካከል ያለው ትስስር እንዲጎለብት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
አርቲስቶቹ በበኩላቸው በፑሽኪን ማዕከል የተመቻቸላቸው ዝግጅት ሁለቱን ሀገራት በባሕል እና በሥነ-ጥበብ ዘርፎች ለማቀራረብ የሚያግዙ ሥራዎች ላይ ለማተኮር እንደሚያነሳሳቸው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X



