“አፍሪካ ውስጥ የተሠራ ምርት በቀጣይ ድንበሮቻችንን አቋርጦ በቀላሉ እንዲንቀሳቀስ ማረጋገጥ ይገባል” - ክቡር ገና
17:50 31.10.2025  (የተሻሻለ: 17:54 31.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
 / ሰብስክራይብ
“አፍሪካ ውስጥ የተሠራ ምርት በቀጣይ ድንበሮቻችንን አቋርጦ በቀላሉ እንዲንቀሳቀስ ማረጋገጥ ይገባል” - ክቡር ገና
በአህጉሪቱ ግዙፉ የጨርቃጨርቅ፣ አልባሳትና የቆዳ ኢንዱስትሪዎች ኤግዚቢሽን የሆነው 11ኛው የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
የዘንድሮው ዝግጅት የአፍሪካ ዲዛይነሮች እና አምራቾችን የፈጠራ መብቶች ለማስጠበቅ እና ፈጠራን ለማበረታታት ሰው ሠራሽ አስተውህሎት እና የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ የትኩረት አቅጣጫዎች ሆነው የሚተዋወቁበት ነው ተብሏል፡፡
"ናይሮቢ የተሠራ ቀሚስ ወደ ዳካር ለመሄድ ለምን ፓስፖርት ያስፈልገዋል? አፍሪካ ውስጥ የተሠራ ምርት ድንበሮቻችንን አቋርጦ በቀላሉ መንቀሳቀስ እንዲችል እናረጋግጥ። ቀጣዩ ዓለም አቀፍ የፋሽን መለያ ከሚላን ወይም ከፓሪስ ሳይሆን ከአዲስ አበባ፣ ከሌጎስ ወይም ከኪጋሊ መምጣት አለበት” ሲሉ የፓን አፍሪካ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ከቡር ገና በኤግዚብሽኑ ላይ ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ውስጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል የገለጹት ክብር ገና፤ ይህንን ለማሳካት የተሻሻለ ሎጂስቲክ፣ የተዋሃዱ የንግድ ፕሮቶኮሎች ብሎም በዲጂታል ክፍያ ስርዓቶችና በመሠረተ ልማት ላይ ኢንቨስትመንት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።
እስከ ጥቅምት 23 በሚቆየው ኤግዚቢሽን ከ210 በላይ ተሳታፊዎች እና ከ70 ሀገራት የተውጣጡ ከ6,000 በላይ ጎብኚዎች እንደሚስተናገዱ ተጠቁሟል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X



