የንጋት ሐይቅን ደህንነት እና ሀብት አጠቃቀም ማስተዳደር የሚያስችል መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ
17:07 31.10.2025 (የተሻሻለ: 17:14 31.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የንጋት ሐይቅን ደህንነት እና ሀብት አጠቃቀም ማስተዳደር የሚያስችል መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ
ሰነዱ የሕዳሴ ግድብ ሐይቅን ከተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ችግሮች ለመከላከል እና በውስጡ ያለውን የዓሳ ሃብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል ሆኖ መዘጋጀቱን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
በመመሪያው የተካተቱ ዝርዝር ጉዳዮች፦
ዓሣ የማስገር ሂደት፣
የዝርያ ማሻሻያ ሥራዎች፣
የዓሣ መረብ አጠቃቀምን ማሻሻል፣
የገበያ ትስስር መፍጠር፡፡
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የምርምር ማዕከላት በመመሪያው አተገባበር ዙሪያ በጥናት የተደገፈ ግብዓት እንዲያቀርቡ አቅጣጫ መቀመጡንም ጠቅሰዋል፡፡
ንጋት ሐይቅ በአሁኑ ወቅት 15 ሺህ ቶን ዓሣ የማምረት አቅም ያለው ሲሆን በዓሣ ማስገር ሥራ በተሠማሩ 78 ማህበራት ውስጥ አባላት ለሆኑ ከ866 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የሥራ እድል ፈጥሯል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X