የዜጎችን ዓመታዊ የወተት ፍጆታ ወደ 200 ሌትር ለማድረስ እየሠራን ነው - የግብርና ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

የዜጎችን ዓመታዊ የወተት ፍጆታ ወደ 200 ሌትር ለማድረስ እየሠራን ነው - የግብርና ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ያስቀመጠውን ዓመታዊ የዜጎች የወተት ፍጆታ አሃዝ ማሳከት በሚያስችል መንገድ ላይ መሆኗን፤ በሚኒስቴሩ የእንስሳት እና ዓሣ ሐብት ልማት ዘርፍ የወተት ሐብት ልማት ዴስክ ኃላፊ ኩሪባቸው እንዳለ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።

"እየተገበርነው ባለነው ሀገር አቀፍ የወተት ሐብት ልማት ስትራቴጂ መሠረት እ.አ.አ በ2031፤ ከ28.4 ቢሊዮን ሊትር በላይ ወተት ለማምረት እየሠራን ነው። የላሞች አመጋገብ፣ ጤና እና የዝርያ ማሻሻል ዋነኛ የትኩረት መስኮቻችን ናቸው" ብለዋል።

ኃላፊዋ በወተት ሐብት ልማት ዙሪያ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራትም አንስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0