የጊኒ-ቢሳው ጦር ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ የተደረገ ሙከራ እንዳከሸፈ ተነገረ

የጊኒ-ቢሳው ጦር ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ የተደረገ ሙከራ እንዳከሸፈ ተነገረ
የጊኒ-ቢሳው ጦር፤ "ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመገልበጥ የተደረገ ሙከራ" ብሎ የገለጸውን ድርጊት እንዳከሸፈና በሴራው ውስጥ ተሳትፈዋል የተባሉ በርካታ ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ በዛሬው ዕለት ማስታወቁን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡
ይህ የተሰማው በሀገሪቱ ለሚካሄደው ቀጣዩ አጠቃላይ ምርጫ የፖለቲካ ቅስቀሳ ሊጀመር አንድ ቀን ሲቀረው ነው፡፡
"ይህ ድርጊት የምርጫ ሂደቱን ለማደናቀፍ ያለመ ነበር" ሲሉ የጦር ኃይሎች ምክትል ዋና አዛዥ ጄኔራል ማማዱ ቱሬ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡
ሆኖም ስንት መኮንኖች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ እና ተከሰተ ስለተባለው ሴራ ዝርዝር መረጃ አልገለጹም፡፡
ከዋና ከተማዋ ቢሳው 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን ወታደራዊ ማሠልጠኛ ማዕከል የሚመሩት ብሪጋዴር ጄኔራል ዳባ ናዋልና፤ ከሴራው ቁልፍ አቀነባባሪዎች አንዱ ናቸው በሚል ከተከሰሱት እና ከታሰሩት ሰዎች መካከል መሆናቸውን ቱሬ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል፡፡
ℹ በጊኒ-ቢሳው፤ ከሕግ አውጪዎች እና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሶስት ሳምንታት በፊት ቅስቀሳ ቅዳሜ ይጀመራል፡፡
የወቅቱ ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኤምባሎ ሐሙስ ከተካሄደው የካቢኔ ስብሰባ በኋላ፤ መንግሥት “ምንም ዓይነት ሁከት አይታገስም” ሲሉ በማስጠንቀቅ፤ “በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የእያንዳንዱን እጩ ደህንነት ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ ወስዷል” ሲሉ ለጋዜጠኞች አረጋግጠዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X