ቻይና ከብሪክስ እና ቁልፍ የባለብዙ ወገን መድረኮች ጋር 'አረንጓዴ' ንግድን ለማስተዋወቅ የሚደረገውን ጥረት ታጠናክራለች - የንግድ ሚኒስቴር

ቻይና ከብሪክስ እና ቁልፍ የባለብዙ ወገን መድረኮች ጋር 'አረንጓዴ' ንግድን ለማስተዋወቅ የሚደረገውን ጥረት ታጠናክራለች - የንግድ ሚኒስቴር
ከ50 በላይ የሚሆኑ ሀገራት በዲጂታል ኢኮኖሚ እና 'አረንጓዴ' ልማት ውስጥ ለቻይና የዓለም አቀፍ ንግድ እና የኢኮኖሚ ትብብር ማዕቀፍ ድጋፍ ሰጥተዋል ሲሉ የሀገሪቱ የንግድ ምክትል ሚኒስትር ሊ ቼንግጋንግ ተናግረዋል።
ምክትል ሚኒስትሩ ያነሷቸው ተጨማሪ ሀሳቦች፦
🟠 ቤጂንግ በእስያ ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ የአካባቢ ጥበቃ ምርቶችን ታሪፍ ቀስ በቀስ ከ5 በመቶ በታች በመቀነስ ግዴታዋን በትጋት እየተወጣች ነው።
🟠 ሀገሪቱ ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተሳለጠ የሁለትዮሽ የንግድ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ የመግባቢያ ስምምነቶችን ስትፈርም ከአካባቢ ብክለት የፀዳ ንግድ ላይ ያተኮሩ ድንጋጌዎችን አካታለች።
🟢 ወደ ሥነ-ምህዳራዊ ሞዴል የሚደረገው ሽግግር "ለልማት ወሳኝ አዝማሚያ እና ለዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ዕድገት ማነቃቂያ" ነው። ነገር ግን ይህ ሂደት በአንዳንድ ሀገራት የንግድ ክልከላ ፖሊሲዎች ምክንያት ተግዳሮቶች ገጥመውታል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በ32ኛው የእስያ ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር የመሪዎች ስብሰባ ላይ ድንበር ተሻጋሪ ንግድን በዲጂታል መንገድ ለማካሄድ እና በንጹህ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማሳደግ ያለሙ ዕቅዶች ይፋ አድርገዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X