በ2018 የአምራች ኢንዱስትሪው ከ12 በመቶ በላይ ዕድገት ያስመዘግባል - የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
15:50 31.10.2025  (የተሻሻለ: 15:54 31.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
 / ሰብስክራይብ
በ2018 የአምራች ኢንዱስትሪው ከ12 በመቶ በላይ ዕድገት ያስመዘግባል - የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
የአምራች ኢንዱስትሪው ዓመታዊ ዕድገት በ2014 ከነበረበት 4.8 በመቶ፤ በ2017 በጀት ዓመት 10.3 በመቶ በመድረስ ኢኮኖሚያዊ አበርክቶ ከዓመት ዓመት እየጨመረ መምጣቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለዘርፉ ቀጣይነት ላለው ዕድገት አስተዋጽኦ ማድረጉን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ፣ ወደ ውጭ የሚላከውን ምርት መጠን መጨመር ላይ የግንዛቤ ለውጥ አምጥቷል ብለዋል፡፡
በንቅናቄው የተከናወኑ ሥራዎች የአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አሳድጓል ማለታቸውን የዘገበው የሀገር ውስጥ ሚዲያ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X