የአፍሪካ የፖሊሲ ነፃነት ከተዋሃደ የክፍያ ስርዓት ይጀምራል - ፀሃፊ
15:36 31.10.2025  (የተሻሻለ: 15:44 31.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
 / ሰብስክራይብ
የአፍሪካ የፖሊሲ ነፃነት ከተዋሃደ የክፍያ ስርዓት ይጀምራል - ፀሃፊ
በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት አሁንም የቅኝ ገዢዎች ጥላ አለ የሚሉት ፀሃፊዋ ሼቮን ፎርድ፤ ለነጻነት እና አንድነታችን ፀር ከሆኑት እነዚህ ፖሊሲዎች ለመላቀቅ መጀመሪያ ሥር መሠረታቸውን መረዳት ይኖርብናል ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
“በክፍያ ስርዓቶች መጀመር እንችላለን፡፡ እያንዳንዱ ሀገር የተለያየ የገንዘብ አይነት አለው፤ ገንዘብ ትልቅ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ ሁሉም የተለየ የክፍያ ስርዓት ስላለው፤ ከናይጄሪያ ሆነህ ደቡብ አፍሪካ ላለ አንድ ሰው ለመክፈል አዳጋች ነው፡፡ በአኅጉሪቱ ለእቃዎች በነፃነት መክፈል እና መላክ የሚቻልበት አንድ የክፍያ ስርዓት እንዲኖረን ማድረግ ለመነሻ ጥሩ ቦታ ይመስለኛል” ሲሉም አብራርተዋል፡፡
የአፍሪካ ሀገራት የምዕራባውያንን የኢኮኖሚ የበላይነት ለመመከት በራሳቸው አቅም የልማት ፕሮጀክቶቻቸውን ማስኬድ እንደሚኖርባቸውም አንስተዋል፡፡
በማሳያነትም ኢትዮጵያ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ያሳካችውን ድል ጠቅሰዋል፡፡
“የእኔ አመለካከት የራሳችንን ፕሮጀክቶች መሸፈን አለብን የሚል ነው። ኢትዮጵያ በቅርቡ ገንብታ ላጠናቀቀችው ግድብ ከምዕራቡ ዓለም ገንዘብ ማግኘት ባለመቻሏ ራሷ መሸፈን ችላለች፡፡ ግድቡን ለመገንባት 14 ዓመታት ቢፈጅባቸውም በራሳቸው መሸፈን ችለዋል፡፡ ስለዚህ የራሳችንን ፕሮጀክቶች ፈንድ ማድረግ እንዳለብን አምናለሁ፤ ገንዘብ ለማግኘት ወደ ምዕራቡ ዓለም መመልከት አያስፈልገንም፡፡"
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X