የኮትዲቯር ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን እንዲፈርስ የተቋሙ ፕሬዝዳንት ጠየቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኮትዲቯር ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን እንዲፈርስ የተቋሙ ፕሬዝዳንት ጠየቁ
የኮትዲቯር ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን እንዲፈርስ የተቋሙ ፕሬዝዳንት ጠየቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.10.2025
ሰብስክራይብ

የኮትዲቯር ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን እንዲፈርስ የተቋሙ ፕሬዝዳንት ጠየቁ

ጥልቅ የሆነ ማሻሻያ አስፈላጊ ነው ያሉት የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ኩሊባሊ-ኩይቢየር፤ ይህም የተቋሙን ሙሉ በሙሉ መፈራረስ ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።

ምርጫዎችን የማዘጋጀት ሥራ ለሌላ አካል መሰጠት አለበት ብለው እንደሚያምኑም አንስተዋል። ኩሊባሊ-ኩይቢየር ለታህሳስ ወር ግዜ ቀጠሮ የተያዘለት የሕግ አውጪዎች ምርጫ በገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽኑ ስር የመጨረሻው ሊሆን እንደሚችል በንግግራቸው ጠቁመዋል።

"በኮትዲቯር ሰላም ለማስጠበቅ አዲስ አሠራር ያስፈልጋል።"

የገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽኑን የማፍረስ ሀሳብ አዲስ አይደለም። ኮሚሽኑ በእያንዳንዱ ምርጫ ወቅት ከፍተኛ ትችት እና ገዥውን ፓርቲ እንደሚደግፍ የሚገልጹ የወገንተኝነት ውንጀላዎች እንደሚሰነዘሩበት የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። በጥቅምት 15ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወቅት ተቃዋሚዎች ተቋሙ እንዲፈርስ በመጠየቅ ተወካዮቻቸው ከኮሚሽኑ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበው ነበር።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0