ፍትሐዊ አቅርቦት ላይ ያነጣጠረ የነዳጅ ምርቶችን የገበያ ድርሻ የሚመራ አዲስ አሠራር ይፋ ተደረገ
13:05 31.10.2025  (የተሻሻለ: 13:14 31.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
 / ሰብስክራይብ
ፍትሐዊ አቅርቦት ላይ ያነጣጠረ የነዳጅ ምርቶችን የገበያ ድርሻ የሚመራ አዲስ አሠራር ይፋ ተደረገ
አዲሱ ሥርዓት ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ፣ ሕዝብ ብዛት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን መሠረት በማድረግ ከተሞችን በሰባት ምድብ ለይቶ አስቀምጧል።
በዚህም አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ያሉ ከተሞች (ገላን፣ ለገጣፎ፣ ሱሉልታ፣ ቡራዩ እና ሰበታ) በምድብ አንድ ስር ሰፍረዋል።
ባህርዳር፣ ሃዋሳ፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ አዳማ፣ ሰመራ ሎጊያ፣ ዲቸቶ እና አይሻ የመሳሰሉት ትላልቅ የክልል ከተሞች በምድብ ሁለት ውስጥ ተካተዋል።
በኢትዮጵያ አሁን ላይ 60 ኩባንያዎች በነዳጅ ማከፋፈል ዘርፍ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል፡፡ ባለሥልጣናት አዱሱ ሥርዓት በዘርፉ ፍትሐዊነትን እንደሚያሰፍን እና በነዳጅ አከፋፋዮች መካከል ፉክክር ላይ የተመሠረተ ግጭትን እንደሚያስቀር ይጠብቃሉ ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X