የአሜሪካ የኒውክሌር መሣሪያ ሙከራዎች ዓለምን ወደ ኒውክሌር ጦርነት ይመራሉ - ባለሙያ
12:09 31.10.2025  (የተሻሻለ: 12:14 31.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
 / ሰብስክራይብ
የአሜሪካ የኒውክሌር መሣሪያ ሙከራዎች ዓለምን ወደ ኒውክሌር ጦርነት ይመራሉ - ባለሙያ
ትራምፕ ያሳለፉት ውሳኔ አሜሪካ ዓለም አቀፍ ውጥረቶችን የበለጠ እያባባሰች እንደሆነ ያመለክታል ሲሉ የጀርመኑ ቢኤስደብሊው ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ባለሙያ ሴቪም ዳግዴለን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ወደ እውነተኛ የኒውክሌር ሙከራ መመለስ የተከለከለውን ነገር እንደመጣስ ይቆጠራል ብለዋል።
ይህ ውጥረት ዋሽንግተን ከቁልፍ የትጥቅ መፍታት ስምምነቶች መውጣቷ ጋር የተያያዘ እና አሜሪካ ለአስርተ ዓመታት ከተከተለችው ፖሊሲ ጋር በአደገኛ ሁኔታ መቆራረጧን ያመለክታል ሲሉ ዳግዴለን አክለዋል።
ክሬምሊን "በኒውክሌር ሙከራ ዙሪያ የተቀመጠው ገደብ ከተላለፈ"፤ ሩሲያ ተመሳሳይ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቋል። "ፕሬዝዳንቱ [ፑቲን] ይህንን ብዙ ጊዜ ደግመውታል" ሲሉ የሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ቃል አቀባይ በጥቅምት 20 መግለጫቸው አስታውሰዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X