አፍሪካ ላይ በታሪክ ለተፈጸሙ አስከፊ እልቂቶች ገንዘብን እንደ ማካካሻ ፍትሕ ማቅረብ ተገቢ አይደለም - የራስ ተፈሪያን እንቅስቃሴ አባል

ሰብስክራይብ

አፍሪካ ላይ በታሪክ ለተፈጸሙ አስከፊ እልቂቶች ገንዘብን እንደ ማካካሻ ፍትሕ ማቅረብ ተገቢ አይደለም - የራስ ተፈሪያን እንቅስቃሴ አባል

ራስ ወልደ ሥላሴ፤ ባሳለፍነው ዓመት የተካሄደው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ፤ "የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካዊያን እና ዘርዓ - አፍሪካውያን" በሚል መሪ ቃል ግዙፍ ጥያቄ ማንሳቱን አውስተዋል፡፡

ሆኖም እርሳቸው አኅጉሪቱ ላይ ለተፈጸሙ አስከፊ እልቂቶች በሒሳብ ስሌት ሊቀርብ የሚችል የገንዘብ ማካካሻ መጠን ሊኖር እንደማይችል ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል፡፡

"በእነ ማርከስ ጋርቬይ ዘመን ወደ ሀገር መመለስ የሚለውን ቃል ነበር የምንጠቀመው፡፡ ይህም ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ንብረታቸውን፣ መሬታቸውን እና ገንዘባቸውን ጭምር ማስመለስ ነው" ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኅብረት ተወካዩ፤ ማካካሻ የሚለው ቃል በአስከፊው እልቂት ፈጻሚዎች የተቀነባበረ ነው የሚል እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0