የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ እና የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በ "ከበባ" ውስጥ ያሉ የዩክሬን ወታደሮችን እንዳያገኙ መከልከሉ፤ በክራስኖአርሜይስክ፣ ዲሚትሮቭ እና ኩፕያንስክ ለሚገኙ ቀሪ የዩክሬን ጦር ኃይሎች የደረሰውን አደጋ አምኖ መቀበል ነው - የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር
11:03 31.10.2025  (የተሻሻለ: 11:04 31.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
 / ሰብስክራይብ
የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ እና የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በ "ከበባ" ውስጥ ያሉ የዩክሬን ወታደሮችን እንዳያገኙ መከልከሉ፤ በክራስኖአርሜይስክ፣ ዲሚትሮቭ እና ኩፕያንስክ ለሚገኙ ቀሪ የዩክሬን ጦር ኃይሎች የደረሰውን አደጋ አምኖ መቀበል ነው - የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር
ኪዬቭ ሚዲያዎች በሩሲያ ኮሪደሮች በኩል ወደ "ከበባው" እንዳይገቡ መከልከሏ፤ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እና የዩክሬንን ሕዝብ ለማታለል አስፈላጊ ነው ሲል ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል፡፡
የኪዬቭ አገዛዝ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፤ ምዕራባውያን ከሩሲያ ጋር ለሚደረገው ጦርነት የሚያፈሱትን ገንዘብ ለመስረቅ እንዲመቻቸው ሁኔታዎችን ለማስጠበቅ እየሞከሩ ነው ሲል ሚኒስቴሩ አክሏል።
እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ፤ በርካታ የዩክሬን ኃይሎች በክራስኖአርሜይስክ፣ ዲሚትሮቭ እና ኩፕያንስክ አካባቢዎች ተከበዋል። ፕሬዝዳንት ፑቲን ሚዲያዎች ሁኔታውን እንዲዘግቡ፤ የሩሲያ ወታደሮች በአካባቢው በግዜያዊነት ጦርነት እንዲያቆሙ ቀደም ብለው ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X