የኤርትራ ፕሬዝዳንት በካይሮ ውይይታቸው የሱዳንን ሉዓላዊነት እንደሚደግፉ በድጋሚ አረጋገጡ
10:34 31.10.2025  (የተሻሻለ: 10:44 31.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
 / ሰብስክራይብ
የኤርትራ ፕሬዝዳንት በካይሮ ውይይታቸው የሱዳንን ሉዓላዊነት እንደሚደግፉ በድጋሚ አረጋገጡ
ከሐሙስ ጀምሮ የአምስት ቀናት ጉብኝት በግብፅ እያደረጉ የሚገኙት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ ከፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ጋር ቀጣናዊ ሰላምን የተመለከተ ውይይት ማካሄዳቸውን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር አስታውቀዋል።
ኤርትራ “በእነዚህ ፈታኝ ጊዜያት ከሱዳን ሕዝብ ጋር በጽናት አብራ እንደምትቆም” ታረጋግጣለች ያሉት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፤ “ውጫዊ ጣልቃገብነት ግጭቱን ከማባባስ ውጪ ምንም አዎንታዊ ውጤት አያስገኝም” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የሱዳንን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ማክበር አስፈላጊ እንደሆነ በማስረገጥ፤ በቀጣናዊ ጥረቶች የሚመራ የሰላም መንገድ መከተል እንደሚገባ አሳስበዋል።
ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ በበኩላቸው ግብፅ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ቁርጠኛ እንደሆነች እና በሱዳን መልሶ ግንባታ ዙሪያ ቁልፍ ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል።
ሁሉም የቀይ ባሕር ዳርቻ ሀገራት አብረው በመሥራት፤ የቀጣናውን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እና ከወሳኝ ሀብቶቹ ተጠቃሚ ለመሆን “አቅሞቻቸውን ማሰባሰብ እና ጥረቶቻቸውን ማስተባበር” ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X