ኡጋንዳ የ2026ቱን ምርጫ ግልጽነት ለማረጋገጥ ዘመናዊ የባዮሜትሪክ የመራጭ መሣሪያዎችን ይፋ አደረገች
21:21 30.10.2025 (የተሻሻለ: 21:24 30.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኡጋንዳ የ2026ቱን ምርጫ ግልጽነት ለማረጋገጥ ዘመናዊ የባዮሜትሪክ የመራጭ መሣሪያዎችን ይፋ አደረገች
የድምፅ መስጫ ወረቀት ከመሰጠቱ አስቀድሞ የመራጮችን ማንነት ለማረጋገጥ የጣት አሻራ እና የፊት ለይቶ ማወቂያ ማሽኖች ጥቅም ላይ ይውላሉ ሲሉ የምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሳይመን ባያባካማ ተናግረዋል፡፡
“እነዚህ እርምጃዎች ስለቴክኖሎጂ ብቻ አይደሉም፤ እያንዳንዱ ድምጽ በትክክልም መራጭን የሚወክል መሆኑን ለማረጋገጥ ነው” ብለዋል።
ይህ ተነሳሽነት የምርጫ ማጭበርበርን ለመቀነስ ያለመው ስትራቴጂ ቁልፍ አካል መሆኑንም ባያባካማ አክለዋል።
የኡጋንዳ ፕሬዝዳንታዊ እና የፓርላማ ምርጫ ጥር 7 ቀን 2018 እንዲካሄድ እቅድ ተይዟል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X