የማዳጋስካር የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ23ቱን ክልሎች አስተዳዳሪዎች ከኃላፊነት አሰናበተ
20:49 30.10.2025 (የተሻሻለ: 20:54 30.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የማዳጋስካር የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ23ቱን ክልሎች አስተዳዳሪዎች ከኃላፊነት አሰናበተ
የአስተዳዳሪዎቹን መሻር ያመላከተው ይፋዊ መግለጫ ለሽግግር ጊዜው በአማራጭነት የቀረቡ ተጨማሪ ዕቅዶች ስለመኖራቸ ያለው ነገር የለም፡፡
ውሳኔው ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊና ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ማክሰኞ በማዳጋስካር አዲስ መንግሥት ከተመሠረተ በኋላ የመጣ ነው። አዲሱ መንግሥት "ሀገሪቱን ከቀውስ ለማውጣት" ኃላፊነት የተሰጣቸው 29 ሚኒስትሮችን አካቷል።
ℹ የአስተዳደሪነት ሹመት 2011 ራጆሊና ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ ሥራ ላይ የዋለ ነበር። ሆኖም በ1996 ክልሎች ሲቋቋሙ፤ ኃላፊዎቻቸው ሁልጊዜም በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣ አዋጅ ይሾሙ ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X