የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናይጄሪያ ትልቁ ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ሆነ
20:28 30.10.2025 (የተሻሻለ: 20:34 30.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናይጄሪያ ትልቁ ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ሆነ
አየር መንገዱ ከጥቅምት 18 ጀምሮ ከአቡጃ ወደ አዲስ አበባ ተጨማሪ ሶስት ሳምንታዊ የምሽት በረራዎችን በማስጀመር አጠቃላይ ቁጥሩን 34 አድርሷል።
“ናይጄሪያን ከ150 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ጋር አገናኝተናል። ለዚህም ኤርባስ ኤ350-1000 እና ቦይንግ 787 ድሪምላይነርን ጨምሮ በዓለም ላይ ካሉት እጅግ ዘመናዊና አዳዲስ አውሮፕላኖች መካከል ቀዳሚዎቹን ተጠቅመናል” ሲሉ በናይጄሪያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስኪያጅ ፍሬህይወት መኮንን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ላይ፦
ወደ ሌጎስ፦ ሁለት ዕለታዊ እና 14 ሳምንታዊ በረራ፣
ወደ አቡጃ፦ 10 ሳምንታዊ በረራ፣
ወደ እኑጉ፦ ሶስት ሳምንታዊ በረራ፣
ወደ ካኖ፦ ሰባት ሳምንታዊ በረራ ያደርጋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ወደ ናይጄሪያ የመጀመሪያውን በረራ ያደረገው ከ65 ዓመታት በፊት በ1952 ነበር፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X