በቀይ ባሕር ጉዳይ ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማደራደር ሩስያ እና ቻይና የተሻለ ዕድል አላቸው - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበቀይ ባሕር ጉዳይ ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማደራደር ሩስያ እና ቻይና የተሻለ ዕድል አላቸው - ባለሙያ
በቀይ ባሕር ጉዳይ ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማደራደር ሩስያ እና ቻይና የተሻለ ዕድል አላቸው - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.10.2025
ሰብስክራይብ

በቀይ ባሕር ጉዳይ ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማደራደር ሩስያ እና ቻይና የተሻለ ዕድል አላቸው - ባለሙያ

በሁለቱ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ውስጥ ሞስኮ እና ቤጂንግ በዲፕሎማሲ፣ በንግድና በወታደራዊ ትብብር መስክ ያላቸው ተሳትፎ እና ተጽዕኖ ድርድሩን ውጤታማ ሊያደርገው እንደሚችል በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት ረ/ፕሮፌሰሩ ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

ይህን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት የሚቀርበው የመፍትሄ ሀሳብ ተደማጭነቱ ከፍተኛ ይሆናል ብለው እንደሚያምኑም አንስተዋል፡፡

“ኤርትራ በማዕቀቦቻቸው ምክንያት አሜሪካ እና በርካታ ምዕራባውያን ሀገራትን እንደ ስጋት ነው የምታያቸው፤ በአንፃሩ ቻይና እና ሩሲያ በሁለቱም ሀገራት ውስጥ አሉ፤ እንደውም ቻይና ኤርትራን የቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ አካል አድርጋታለች፤ ከኢትዮጵያ ጋርም ሁኔታ የማይፈታው ስልታዊ ትብብር እና ወዳጅነት በ2015 መስርታለች፡፡ በዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ትብብር ዘርፍ ሩሲያ ያላት አጋርነትም ተጠቃሽ ነው” ብለዋል፡፡

ሩሲያ እና ቻይና ከሁለቱ ሀገራት ጋር ያላቸውን ተዓማኒ የፖለቲካ ግንኙነት በመጠቀም ማደራደር ከቻሉ አሁን ያለውን ውጥረት ማርገብ እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኘተው አሜሪካ፣ ቻይና፣ ሩሲያ፣ አውሮፓ እና አፍሪካ ኅብረት በቀይ ባሕር ዙሪያ የማደራደር ሚና እንዲኖራቸው መጠየቃቸው የሚታወስ ነው፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0