ኢትዮጵያ ለክሪፕቶ ማይኒንግ አዲስ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ይፋ አደረገች
19:05 30.10.2025 (የተሻሻለ: 19:14 30.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለክሪፕቶ ማይኒንግ አዲስ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ይፋ አደረገች
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለዘርፉ ደንበኞች ከህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የተሻሻለ ክፍያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
አዲሱ ማሻሽያ፤ የጊዜ አጠቃቀም ሥርዓትን መሠረት ያደረገ የታሪፍ ማስተካከያ አሠራርን የሚዘረጋ ነው፡፡
የአጠቃቀም ሰዓቱ በሶስት የተዋቀረ ሲሆን፦
የከፍተኛ ፍጆታ ሰዓታት ከምሽቱ 12:00 እስከ ምሽቱ 4:00፤ ከ0.06 የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ በከፍተኛ ዋጋ የሚሰላ፣
የመካከለኛ ፍጆታ ሰዓታት ከጠዋቱ 3:00 እስከ ምሽቱ 12:00፤ ከ0.035 የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ የሚሰላ፣
የዝቅተኛ የፍጆታ ሰዓታት ከምሽቱ 5:00 እስከ ንጋቱ 11:00 ከ0.035 የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ የሚሰላ፡፡
አዲሱ ታሪፍ እስከ ሐምሌ 2020 ዓ.ም ድረስ ዓመታዊ የዋጋ ጭማሪ እንደሚደረግበት ተቋሙ አስታወቋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፈው በጀት ዓመት ከአጠቃላይ ሽያጭ 18 በመቶውን ለዳታ ማይኒንግ ዘርፍ በማቅረብ፤ 220 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ስለማግኝቱ መግለፁ ይታወሳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X